የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተስፋየ አድማሱ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ እናንተን አሰልጥነን መተዉ ሳይሆን በተለያየ ነገር ድጋፍ ማድረግ ጭምር ነው ብለዋል ።
በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከGIZ ጋር በመተባበር ሰልጥነው የተመረቁ ሰልጣኞች በቡድን በመደራጀት በዛሬው ዕለት በኢንኩቤሽን ማዕከል የስራ ፈጠራ ውድድር አድርገዋል።
ከንግድ ሀሳብ ከማበልጸግ ጀምሮ በኮሌጁ ኢንኩቤሽን ማዕከል ድጋፍ ተደርጎላቸው የፈጠራ የንግድ ሀሳባቸውን ካበለጸጉ በኋላ በዛሬው ዕለት አዲስ የንግድ ስራ የፈጠራ ውድድር አድርገዋል።
በ 11 የስራ ፈጠራ ሀሳብ ላይ ውድድር አድረገው ውድድሩን በበላይነት ያጠናቁት ፅናት የጋርመንት ሰልጣኞች ሲሆኑ 2ኛ ደረጃ ሀሴት የንጽህና መጠበቂያ እና በ3ኛ ደረጃ እንደቤቱ በፈረኒቸር ስራ አሸናፊ ሆኗል።
የዛሬው ዉድድር ለ11 ዱ የፈጠራ ሀሳብ ተወዳዳሪዎች 407,000 የኢትዩጵያ ብር ተጠቃሚ መሆኑ ልዩ ያደረገዋል።
በመጨረሻም የኮሌጁ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት ም/ዲን አቶ መሀመድ ጠይብ ገንዘቡ ብቻ በቂ አደለም ሀሳቡን እና ተነሳሽነቱን ማስቀጠል መቻል አለበት አሁን ላይ ያቀረባችሁት ብቻ በቂ ሳይሆን በቲም በመመካከር መረጣችሁ በተማራችሁበት ይሁን አይሁን ስኬታማ በመሆን ለሀገረም ለራሳችሁም በሚደረግላቸው ድጋፍ ራሳቸውን እና ሐገራቸውን በኢኮኖሚ እንዲያሳድጉ እና ችግር ፈቺ ምርቶችን እንዲያመርቱ መልዕክት አስተላልፈዋል ። አቶ መሀመድ አክለዉም " ህልመኛ" መሆን ያስፈልጋል ብለዋል ።
ተግባረዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ህዳር 24/2018/ዓ.ም
.