ተግባረዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ሀምሌ 4/2017/ዓ.ም
ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቴክኖሎጅ ልማትእና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት የዘረፋን የ2017 በጀት አመት የማጠቃለያ ሪፖርት አቀረቡ ።
ሪፖርቱን የየዘረፋን ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ፣ ኢንኩቬሽን ፣ቴክኖሎጂ ልማት እና ጥናት እና ምርምር በእቅዳቸው መሰረት የተከናወኑ ተግባራትን ፣ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ የመፍትሄ ሀሳቦችን እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ያካተተ ሪፖርት አቅርበዋል ።
በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ማለትም የስልጠና ሂደትን፣ የተቋማዊ ሪፎርም ትግበራን እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ የተገኙ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የያዘ ሪፖርት አቅርበዋል።
በተጨማሪም በሪፖርቱ ላይ የተገኙ ሰራተኞች ከተቋሙ ቀጣይ እቅዶች እና ከአሰራር ማሻሻያዎች ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተው ከአመራሮች ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቷቸዋል።
ተግባረዕድ ኮሚዩኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት