የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 የበጀት ዓመት የተከታታይ 12 ወራት የዕቅድ አፈጻፀም ሪፖርት በዛሬው ዕለት ሁሉም የኮሌጁ ማኅበረሰብ በተገኘበት አቀረበ::
ሪፖርቱን አቶ ደረሰ ጌታቸው የስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዩች ም/ዲን ፣አቶ ግሩም ቃል ዘነበ የኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት አስተባባሪ እና አቶ ወንዱ ለሜሳ የተቋማት ልማት የአቅም ግንባታ ጉዳዩች ም/ዲን አቅርበዋል ።
ወ/ሮ ዘነቡ ዘረአብሩክ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የ2018እቅድ አቅርበዋል::
የኮሌጁ ማኅበረሰብ በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት፣ ሐሳብ አስተያየት እና በቀጣዩ በ2018 የበጀት ዓመት ሊሻሻሉ ይገባቸዋል ያሏቸውን ሐሳቦችን አቅርበዋል::
በቀረበዉ ሀሳብ አስተያየት ጥያቄዎች ላይ አመራሮች ምላሽ ሰጥተዋል ።
የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተስፋዬ አድማሱ "ኮሌጁ በ2017 የበጀት ዓመት አንጋፋነቱን ያስመሰከሩ ሰፊ ስራዎችን ተሰርቷል:: ይሕ ጥንካሬው በከተማ ደረጃ በክሕሎት: በቴክኖሎጂ እና በጥናትና ምርምር ውድድር ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል" ያሉ ሲሆን ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት ለ2018 የበጀት ዓመት ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል::
ዛሬ የቀረበው ሪፖርት በዚህ ደረጃ ከመገምገሙ በፊት በስራ ክፍል ደረጃ ፣ በፕሮሰስ ካውንስሉ እና በጠቅላላ ካውንስል በሚገባ ተገምግሞ እንደነበር የሚታወስ ነው።
ተግባረ ዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን
ሀምሌ 9/2017/ዓ.ም