User Manual "በ E- School ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሔደ::"

"በ E- School ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሔደ::"

02nd July, 2025

ሰኔ 25/ 2017 ዓ/ም ተግባረ ዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን

በአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለአሰልጣኞች: ለስልጠና ዘርፍ ኃላፊዎች: ለማስተባበሪያ ክፍሎች: ለኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አስተባባሪዎች እና ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት በE- School ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል::

አቶ ተስፋዬ አድማሱ (የኮሌጁ ዋና ዲን) "ያስቀመጥነውን ራዕይ ለማሳካት ይሕንን ስርዓት መተግበር አለብን" ያሉ ሲሆን ቀሪ ስራዎችን አጠናቆ ሙሉ በሙሉ እስከ ሰኔ 30 መተግበር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል::

አቶ ደረሰ ጌታቸው (የስ/አካ/ጉ/ም/ዲን) "ለሰልጣኞ ጭምር ግንዛቤ በማስጨበጥ ወረቀት አልባ ተቋም ማድረግ አለብን" ብለዋል::

የአዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2022 በዲጂታል የበለፀገ ተቋምን እውን ለማድረግ እየሰራ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ ነው::

ተግባረ ዕድ ኮሚዩኒኬሽን እና ሕዝብ ግንኙነት

.

Copyright © All rights reserved.

Created with