የብቃትና ስራ ትስስር አተያዮች (QEP) ፕሮጀክት ግምገማ ተከናወነ፡፡
ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በጀርመን የልማት ትብብር ሚኒስቴር ደጋፊነት ባለፉት ስድስት ዓመታት ሲተገበር የቆየው በተለይ ስደተኞችን፤ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እንዲሁም ሌሎች ስልጠና ፈላጊዎችን በአጫጭር ስልጠና በማብቃት የስራ ትስስር ሲፈጥር የቆየውን ፕሮጀክት አፈፃፀም በስቲሪንግ ኮሚቴው ተገምግሟል፡፡

በግምገማው በትግራይ፤ በቤሻንጉል፤ በጋምቤላ እና በሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጀመሪያው ዙር የስልጠና፤ የስራ ትስስር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ የፕሮጀክቱ የልማት ስራ አፈፃፀሞች በዝርዝር በቢሮ ሃላፊዎቹ ሪፖርት ቀርቦ የታየ ሲሆን፤ የሌሎችም የኮሚቴው አባላት ለፕሮጀክቱ አፈፃፀም የነበራቸው ሚና በተወካዮቹ አማካኝነት እዲቀርብ ተደርጓል፡፡ ከቀረቡት ሪፖርቶቹም መሰድ የሚገባቸው በርካታ መልካም ተሞክሮዎች የተገኙ ስለመሆኑ መረዳት ተችሏል፡፡
በመቀጠልም የሁለተኛውን ዙር የፕሮጀክት ይዘትና መርሃግብር በጂ አይ ዚ ፕሮግራም ማኔጀር ፒር ጁበርት አማካኝነት ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገበት በኃላ፤ በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ እና የኮሚቴው ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ አማካኝነት ዝርዝር አቅጣጫ ተሰቶበት የዕለቱ መርሃግብር በአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የመስክ ጉብኝት ተጠናቋል፡፡
በመድረኩ የስራና ክህሎት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እና የስራ ስምሪት ሚኒስትር ዲኤታዎች፤ የስደተኞና ተመላሾች አገልግሎት፤ አዲስ አበባን ጨምሮ የአራቱም ክልሎች የቢሮ ሃላፊዎች፤ ከጀርመን ኢምባሲ፤ ከ ኬኤፍ ደብሊው እና ጂ አይ ዚ ልዩ ልዩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተውበታል፡፡